በርካታ ነገሮች በነዳጅ የዋጋ አወጣጥ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ዋና ዋናዎቹን እንዘርዝር።
- አቅርቦት እና ፍላጎት። ምናልባትም በጣም አስፈላጊው ምክንያት ነው። የተለመደው የአቅርቦት እና የፍላጎት ህግ፦ ለነዳጅ ያለው ፍላጎት ካለው አቅርቦት ሲበልጥ፣ ዋጋዎች የመጨመር አዝማሚያ ይኖራቸዋል። በተቃራኒው፣ ከመጠን በላይ አቅርቦት ሲኖር፣ ዋጋዎች የመቀነስ አዝማሚያ አላቸው።
- የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (OPEC) ውሳኔዎች። ነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (OPEC) የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርትን ጉልህ ድርሻ የሚቆጣጠር ካርቴል ነው። በምርት ደረጃዎች ላይ የሚሰጡት ውሳኔዎች በነዳጅ ዋጋዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት ከቀነሰ፣ የኦፔክ+ (OPEC+) አገራት የነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ሊስማሙ ይችላሉ፣ ይህ ደግሞ በነዳጅ ገበያ ላይ ያለውን አቅርቦት በመቀነስ የዋጋ ቅነሳውን ያስቆማል።
- የኢኮኖሚ ሁኔታዎች። የዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ሁኔታም በነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ኢኮኖሚው እያደገ ሲሄድ፣ ለነዳጅ ያለው ፍላጎት የመጨመር አዝማሚያ ይኖረዋል፣ ይህ ደግሞ ዋጋን ከፍ ያደርጋል። በተቃራኒው፣ ኢኮኖሚው በሚታገልበት (በሚዳከምበት) ጊዜ፣ ለነዳጅ ያለው ፍላጎት ይቀንሳል፣ ይህም ዋጋዎች እንዲያሽቆለቁሉ ያደርጋል። ለምሳሌ፣ የኮቪድ (Covid) ክልከላዎች ከተነሱ በኋላ አሁን ብዙ ተንታኞች የቻይና ፍላጎት ይጨምራል ብለው ይጠብቃሉ። በገበያው ውስጥ በቂ አቅርቦት አለ፣ ስለዚህ በፍላጎት ላይ የሚታይ ጭማሪ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል።
- የጂኦፖለቲካዊ ክስተቶች። በዋና ዋና ነዳጅ አምራች ክልሎች ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ጦርነቶች እና ግጭቶች አቅርቦትን ሊያስተጓጉሉ እና ዋጋዎች እንዲጨምሩ ሊያደርጉ ይችላሉ። ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ የአውሮፓ አገራት የሩስያን ነዳጅ መቀበል ባለመፈለጋቸው እና አቅርቦቶች በመስተጓጎላቸው የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ሌላ ምሳሌ። በኮቪድ-19 ወቅት፣ ብዙ ኢኮኖሚዎች መዘጋት ጀመሩ፣ እና ሰዎች ብዙም አለመንቀሳቀስ (አለመጓዝ) ጀመሩ። አቅርቦት ከፍተኛ ሆኖ ሳለ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ወድቆ ነበር። ይህም የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት እንዲቀንስ አድርጓል።
- የተፈጥሮ አደጋዎች። እንደ አውሎ ነፋሶች እና የመሬት መንቀጥቀጦች ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች የነዳጅ ምርትን እና ትራንስፖርትን ሊያስተጓጉሉ ስለሚችሉ ዋጋዎች እንዲጨምሩ ያደርጋሉ። ለምሳሌ፣ በአየር ሁኔታ ምክንያት የሚፈጠሩ የቧንቧ መስመር መቆራረጦች የነዳጅ አቅርቦቶችን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ። በአቅርቦት ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል ማለት የአቅርቦት መቀነስ ነው። ፍላጎት ከፍተኛ ሲሆን የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል።
- የገንዘብ ምንዛሬ መጠኖች። ነዳጅ በተለምዶ ዋጋው የሚተመነው በአሜሪካ ዶላር ስለሆነ፣ የምንዛሬ ተመኖች መዋዠቅ በሌሎች አገራት ላሉ ገዢዎች የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
እናጠቃልለው፡ ጠንካራ ፍላጎት እና የተወሰነ አቅርቦት ሲኖር፣ እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ምርትን በሚያስተጓጉሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ጊዜ የነዳጅ ዋጋ የመጨመር አዝማሚያ አለው። በተቃራኒው፣ በደካማ ፍላጎት፣ ከመጠን በላይ አቅርቦት እና በተረጋጉ የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት የነዳጅ ዋጋ የመቀነስ አዝማሚያ አለው።
መልካም ንግድ ይሁንልዎ
