ሸቀጦችን ይገበያዩ
በተሻሉ ሁኔታዎች
የንግድ ፖርትፎሊዮዎን እንደ ወርቅ፣ ብር እና ነዳጅ ባሉ መሪ ሸቀጦች በ JustMarkets ያስፋፉ።

ለምን በ JustMarkets ሸቀጦችን ይገበያያሉ?
የሚመርጡትን ማንኛውንም የንግድ ስልት በመጠቀም ሸቀጦችን በልበ ሙሉነት ይነግዱ።
የሸቀጦች ውጤቶች (ኮሞዲትይ ደሪቫቲቭስ)
እንደ ወርቅ፣ ብር እና የተለያዩ የኃይል ምንጮች ባሉ ታዋቂ ሸቀጦች አማካኝነት የኢንቨስትመንት ስልትዎን ያብዙ (ያስፉ)።
ተስማሚ ንግድ
ለተሻሻለ የንግድ አፈጻጸም ሳምንቱን ሙሉ ወርቅ (XAUUSD)፣ ብር (XAGUSD) እና ነዳጅ በመገበያየት ወደ ሸቀጦች ገበያ በቀላሉ ይግቡ።
የኢንቨስትመንት ደህንነት
ከዜሮ በታች ከሚሆን ቀሪ ሂሳብ ጥበቃ ጋር በሸቀጦች ላይ ኢንቨስት ያድርጉ። በገበያው ላይ በሚፈጠር ፈጣን እንቅስቃሴ ምክንያት ከዜሮ በታች ቀሪ ሂሳብ ሲያጋጥም፣ ደንበኞችን ካልተጠበቀ ኪሳራ ለመጠበቅ ሲባል ሂሳቡ ወደ ዜሮ ይቀየራል።
የዋጋ መዛባት (Slippage) ጥበቃ
በ ከዋጋ መዛባት (slippage) ጥበቃችን ያለ ምንም ስጋት ይገበያዩ። የዋጋ መዛባቶችን (slippages) ይከላከላል፣ ስለዚህ ምንም አይነት አነስተኛ የዋጋ ለውጦች ሳያመልጡዎት ግብይቶችዎ እርስዎ በጠበቁት ቦታ ይጀምራሉ እንዲሁም ያበቃሉ።
ዝቅተኛ እና የተረጋጋ የዋጋ ልዩነቶች (spreads)።
በገበያው መዋዠቅ ጊዜም ቢሆን መረጋጋትን በማረጋገጥ፣ ከ 0.2 ፒፕስ በሚጀምር እጅግ በጣም ጠበብት ስፕሬድ ወርቅ፣ ብር ወይም ነዳጅ ይገበያዩ።
ፈጣን የትዕዛዝ አፈጻጸም
በ JustMarkets የግብይት ስምምነቶችዎ ወዲያውኑ በሚባል ደረጃ ይፈጸማሉ። በአንድ ሰከንድ ሽርፍራፊዎች ውስጥ ግብይቶችዎ መፈጸማቸውን እናረጋግጣለን ይህም ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመገበያየት የሚፈልጉትን ፍጥነት ይሰጥዎታል።
የሸቀጦች ገበያ ስፕሬድስ (spreads) እና ስዋፕስ (swaps)
የሸቀጦች ገበያ ሁኔታዎች
የሸቀጦች ገበያ እንደ የከበሩ ማዕድናት እና የኃይል ምንጮች ያሉ የተለያዩ ሸቀጦችን ለመገበያየት የሚያስችል ዓለም አቀፍ የገበያ ቦታ ነው። ግብይት የሸቀጡ ዋጋ ወደ ላይ እየወጣም ሆነ ወደ ታች እየወረደ፣ ዋናውን ንብረት መግዛት ሳያስፈልግ እንደ ወርቅ እና ነዳጅ ያሉ ከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ ያላቸውን መሳሪያዎች ዋጋ ለመገመት ያስችላል።
የንግድ ሰዓታት
የሸቀጦች ገበያ ከሰኞ 01:02 እስከ አርብ 23:59 ድረስ ክፍት ሲሆን፣ የተወሰኑ ጥንዶች ግን የራሳቸው የሆነ የተለየ የጊዜ ሰሌዳ አላቸው። ለተወሰኑ የመክፈቻ ሰዓታት የሚከተለውን ይመልከቱ፦
| መሳሪያ | መክፈቻ | መዝጊያ |
| XAGEUR, XAUAUD, XAUEUR, XPDUSD, XPTUSD, XAGUSD, XAUUSD | ሰኞ 01:02 እለታዊ እረፍት 23:58 – 01:01 |
አርብ 23:58 |
| WTI, XNGUSD | ሰኞ 01:02 እለታዊ እረፍት 23:59 – 01:02 |
አርብ 23:59 |
| BRENT | ሰኞ 03:02 እለታዊ እረፍት 23:59 – 03:02 |
አርብ 23:59 |
ሁሉም የጊዜ ሰሌዳዎች በሰርቨር ሰዓት አቆጣጠር (GMT+3)ናቸው።
ስፕሬዶች (Spreads)
በሸቀጦች ገበያ ውስጥ ያሉ ስፕሬዶች በየጊዜው ተለዋዋጭ ናቸው። ከላይ የተጠቀሱት ስፕሬዶች ካለፉት የግብይት ቀናት የተወሰዱ አማካዮች ናቸው። ወቅታዊ የሆኑ ስፕሬዶችን ለማየት የእኛን ፕላትፎርም ይመልከቱ።
ሊኩዲቲ በሚቀንስበት ወቅት ስፕሬዶች ሊጨምሩ ይችላሉ። ይህ እንደ ዕለታዊ እረፍቶች ያሉ ጊዜያትን የሚያካትት ሲሆን መደበኛ ሁኔታዎች እስኪመለሱ ድረስ ሊቀጥል ይችላል።
የእኛ ምርጥ ስፕሬዶች የተረጋገጡት በሮው አካውንታችን ላይ ሲሆን፣ ስፕሬዶቹም ከ 0.2 ፒፕስ ይጀምራሉ።
ከስዋፕ-ነፃ ግብይት
ስዋፕ ማለት በአዳር ክፍት ሆነው በሚቆዩ የንግድ ፖዚሽኖች (ትዕዛዞች) ላይ የሚታሰብ የወለድ ክፍያ ነው። የስዋፕ መጠኖች በተለያዩ የንግድ ጥንዶች ላይ ይለያያሉ። ፖዚሽኑ እስኪዘጋ ድረስ ስዋፖች ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር በየቀኑ በ 22፡00 GMT+2 ሰዓት ላይ ይተገበራሉ። የየሳምንቱ መጨረሻ (ቅዳሜና የእሁድ) የገንዘብ ወጪዎችን ለማካካስ ሲባል ረቡዕ እለት የሚታሰቡ ስዋፖች በሶስት እጥፍ የሚጨምሩ መሆኑን ልብ ማለት አስፈላጊ ነው።
ከስዋፕ-ነፃ ሁኔታ ካለዎት፣ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ “የተራዘመ ስዋፕ-ነፃ ይገኛል” ተብለው ምልክት በተደረገባቸው መገበያያ መሳሪያዎች ላይ ክፍያ አይጠየቁም።
ከየትኛውም ሀገር ያሉ ሁሉም የደንበኛ አካውንቶች በራስ-ሰር ከስዋፕ-ነፃ ሁኔታ ይሰጣቸዋል።
ከስዋፕ ነፃ የሆነ ግብይት ለሚከተሉት መሳሪያዎች አይገኝም፦ XNGUSD፣ WTI፣ BRENT።
የማቆሚያ ደረጃ (Stop level)
የማቆሚያ ደረጃ (stop level) ማለት ተጠባባቂ ትዕዛዝን (የኪሳራ ማቆሚያ (Stop Loss)፣ የትርፍ መውሰጃ (Take Profit)፣ መግዛት/መሸጥ ማቆሚያ (Buy/Sell Stop)፣ የመግዛት/መሸጥ ገደብ (Buy/Sell Limit)) በሚያስገቡበት ጊዜ በሚፈለገው የግብይት መክፈቻ ዋጋ እና አሁን ባለው (የገበያ) ዋጋ መካከል ያለው አነስተኛው ተቀባይነት ያለው ርቀት ነው። የማቆሚያ ደረጃው በገበያ ተለዋዋጭነት ጊዜያት የዋጋ መዛባት (slippage) አደጋ ለመቀነስ ይረዳል፣ እንዲሁም ተጠባባቂ ትዕዛዞች ይበልጥ አስተማማኝ በሆነ መንገድ እንዲፈጸሙ ያረጋግጣል።
ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተመለከቱት የማቆሚያ ደረጃ (stop level) እሴቶች ተለዋዋጭ መሆናቸውን እና የተወሰኑ የከፍተኛ ድግግሞሽ ስልቶችን ለሚተገብሩ ወይም የኤክስፐርት አማካሪዎችን ለሚጠቀሙ ነጋዴዎች ላይገኙ እንደሚችሉ ትኩረት ይስጡ።
ቋሚ የማርጂን መስፈርቶች
ለሸቀጦች ግብይታችን የማርጂን መስፈርቶች ቋሚ ናቸው፤ ነገር ግን እንደየ ሌቨሬጅዎ ሊለወጡ ይችላሉ። ሊያገኙት የሚችሉት ከፍተኛው ሊቨሬጅ በ አካውንትዎ ውስጥ ባለው የገንዘብ መጠን (equity) ላይ ተመስርቶ ይለያያል።
- ለ XAUUSD፣ XAGUSD፣ XAGEUR፣ XAUEUR እና XAUAUD ከፍተኛው ሌቨሬጅ 1:3000 ሆኖ ተቀምጧል።
- ለ XPDUSD እና XPTUSD ሊቨሬጅ 1:100 ሆኖ ተቀምጧል።
- ለ BRENT፣ WTI እና XNGUSD ሊቨሬጅ 1:200 ሆኖ ተቀምጧል።
የማርጂን መስፈርቶች ከፍተኛ ማርጂን ከሚጠየቅባቸው የተወሰኑ ጊዜያት ውጭ ሁልጊዜም ቋሚ ሆነው ይቆያሉ።
ተለዋዋጭ የማርጂን መስፈርቶች
የአካውንትዎ የማርጂን መስፈርት በሚመርጡት የሌቨሬጅ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። የእርስዎን ሌቨሬጅ ማስተካከል በማርጂን መስፈርቶችዎ ላይ ተመጣጣኝ ለውጦችን ያስከትላል። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ስፕሬዶች በገበያ ሁኔታዎች ላይ ተመስርተው እንደሚለዋወጡ ሁሉ፣ ለእርስዎ የሚገኘው ሌቨሬጅም ሊለወጥ ይችላል። ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡ በርካታ ምክንያቶች ለእነዚህ ለውጦች ሊዳርጉ ይችላሉ።
ሌቨሬጅ
ከፍተኛው ሌቨሬጅ በአካውንትዎ ላይ ባለው ጠቅላላ የተጣራ ገንዘብ (equity) ላይ በመመስረት ይለወጣል፦
| ጠቅላላ የተጣራ ገንዘብ (Equity) ፣ በአሜሪካ ዶላር (USD) | ከፍተኛው ሌቨሬጅ |
| 0 – 999 | 1:3000 |
| 1,000 – 4,999 | 1:2000 |
| 5,000 – 29,999 | 1:1000 |
| 30,000 ወይም ከዚያ በላይ | 1:500 |
የኃይል ምንጮች እንደየ ባህሪያቸው የተለያየ ከፍተኛ ሌቨሬጅ አላቸው።
የኢኮኖሚ ዜናዎች
ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የኢኮኖሚ ዜናዎች ከመታተማቸው 15 ደቂቃዎች በፊት ጀምሮ እስከ 5 ደቂቃዎች በኋላ ድረስ፣ ተጽዕኖ በሚያርፍባቸው የግብይት መሳሪያዎች ላይ ለሚከፈቱ አዳዲስ ግብይቶች የማርጂን መስፈርቶች በተቀነሰ ከፍተኛ ሌቨሬጅ ይሰላሉ።
ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዜናዎች መቼ እንደሚወጡ በእኛ የኢኮኖሚ የቀን መቁጠሪያ ላይ ማወቅ ይችላሉ።
የገበያ ሽግግሮች፣ የሳምንት መጨረሻ ቃናት (ቅዳሜ እና እሁድ) እና የበዓል ቀናት
የጨመረ የማርጂን ህግ በገበያ ሽግግሮች፣ በሳምንት መጨረሻ ቃናት (ቅዳሜ እና እሁድ) እና በህዝባዊ በዓል ቀናት በአንዳንድ የግብይት መሳሪያዎች ላይም ተፈጻሚ ይሆናል። በእነዚህ ወቅቶች እነዚህ መሳሪያዎች ለዝቅተኛ ሌቨሬጅ የተጋለጡ ናቸው።
ስለ ከፍተኛ የማርጂን መስፈርቶች እዚህ የበለጠ ያንብቡ።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
1
ሸቀጦች ምንድን ናቸው?
ሸቀጦች ማለት ሊገዙ እና ሊሸጡ የሚችሉ ጥሬ እቃዎች ወይም ቀዳሚ የግብርና ምርቶች ናቸው። እነዚህም እንደ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ያሉ የኃይል ምንጮችን፣ እንደ ወርቅ፣ ብር እና መዳብ ያሉ ማዕድናትን፣ እንዲሁም እንደ ስንዴ፣ ቡና እና ስኳር ያሉ የግብርና ምርቶችን ያካትታሉ። ሸቀጦች በንግድ ውስጥ የሚያገለግሉ መሰረታዊ እቃዎች ሲሆኑ፣ በአብዛኛው ለበለጠ ውስብስብ እቃዎች እና አገልግሎቶች መገንቢያ መሰረቶች ናቸው።
2
በሸቀጦች ገበያ ውስጥ ምን ዓይነት መሳሪያዎችን መገበያየት ይቻላል?
በሸቀጦች ገበያ ውስጥ የፊውቸርስ ኮንትራቶችን ፣ ኦፕሽንስ፣ የልውውጥ ንግድ ፈንዶችን (ETFs) እና የልዩነት ኮንትራቶችን (CFDs) ጨምሮ የተለያዩ መሳሪያዎችን መገበያየት ይችላሉ። እነዚህ መሳሪያዎች ነጋዴዎች ሸቀጦቹን በአካል መያዝ ሳያስፈልጋቸው የዋጋ እንቅስቃሴያቸውን እንዲገምቱ ያስችሏቸዋል።
3
በዓለም ላይ በብዛት የሚሸጠው ሸቀጥ ምንድን ነው?
በዓለም ላይ በብዛት የሚሸጠው ሸቀጥ ድፍድፍ ነዳጅ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁልፍ የኃይል ምንጭ ሲሆን በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የዋጋ መዋዠቁ በዓለም ገበያዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር፣ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይ እና የሚገበያይ ሸቀጥ ያደርገዋል።
4
ኢንቨስት ለማድረግ ምርጥ 3 ሸቀጦች የትኞቹ ናቸው?
ኢንቨስት ለማድረግ ምርጥ ሶስት ሸቀጦች አብዛኛውን ጊዜ ድፍድፍ ነዳጅ፣ ወርቅ እና የተፈጥሮ ጋዝን ያካትታሉ። እነዚህ ሸቀጦች በሰፊው ጥቅም ላይ በመዋላቸው፣ በገበያ ላይ ባላቸው ሊኩዲቲ እና በሚያሳዩት የዋጋ መለዋወጥ (volatility) ምክንያት ትርፍ ለማግኘት ሰፊ ዕድሎችን ስለሚፈጥሩ ይታወቃሉ።
5
በሸቀጦች ላይ ኢንቨስት ማድረግ የምጀምረው እንዴት ነው?
በሸቀጦች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለመጀመር በመጀመሪያ ስለ ሸቀጦች ገበያ እና የሸቀጦችን ዋጋ ስለሚወስኑ (ተጽዕኖ ስለሚያደርጉ) ምክንያቶች እራስዎን ያስተምሩ። እንደ ፊውቸርስ ወይም የልዩነት ኮንትራቶች (CFDs) ያሉ የሸቀጦች ንግድን የሚያቀርብ የብሮከሬጅ አካውንት ይክፈቱ። ለመለማመድ በዴሞ አካውንት ይጀምሩ እና አንዴ ልምዱን ካዳበሩ በኋላ መጀመሪያ ላይ በአንድ ወይም በሁለት ሸቀጦች ላይ ብቻ በማተኮር በእውነተኛ ገንዘብ መገበያየት መጀመር ይችላሉ።
6
ወርቅን እንደ ሸቀጥ የምገዛው እንዴት ነው?
ወርቅን እንደ ሸቀጥ ለመግዛት፣ በብሮከሬጅ አካውንት በኩል በወርቅ ፊውቸርስ፣ በወርቅ ETFs ወይም በወርቅ CFDs ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ። በተጨማሪም አካላዊ ወርቅን በአሞሌዎች (bars) ወይም በሳንቲም መልክ ታማኝ ከሆኑ አቅራቢዎች መግዛት ይችላሉ። እያንዳንዱ ዘዴ እንደ አካላዊ ወርቅን ማከማቸት ወይም የወርቅ CFDs ሌቨሬጅን እንደመረዳት ያሉ የራሱ የሆኑ ጥቅሞች እና ጥንቃቄዎች አሉት።
7
በሸቀጦች ገበያ ንግድ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ስጋቶች ምንድን ናቸው?
የሸቀጦች ገበያ ንግድ ዋና ዋና ስጋቶች የገበያ መዋዠቅን፣ ጂኦፖለቲካዊ ስጋቶችን፣ የአቅርቦት እና የፍላጎት ተለዋዋጭነትን፣ የምንዛሬ መዋዠቅን እና የአየር ንብረት ሁኔታዎች በግብርና ሸቀጦች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ያካትታሉ። ነጋዴዎች ከሌቨሬጅ እና ከማርጂን ንግድ ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ማወቅ አለባቸው።
8
ለተጠባባቂ ትዕዛዞች፣ ኪሳራ ማስቆሚያ (SL) እና ትርፍ መውሰጃ (TP) የእርስዎ ሕጎች ምንድን ናቸው?
በሸቀጦች ንግድ ውስጥ፣ ተጠባባቂ ትዕዛዞች አስቀድሞ በተወሰነ ዋጋ ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ይቀመጣሉ። የኪሳራ ማስቆሚያ (SL) ትዕዛዞች አንድን የንግድ ፖዚሽን በተወሰነ የዋጋ ደረጃ ላይ በመዝጋት ሊከሰቱ የሚችሉ ኪሳራዎችን ለመገደብ ይረዳሉ። የትርፍ መውሰጃ (TP) ትዕዛዞች ዋጋው ምቹ ደረጃ ላይ ሲደርስ ንግዱን በራስ-ሰር በመዝጋት ትርፎችን ያስጠብቃሉ። የኪሳራ ማስቆሚያ (SL) እና የትርፍ መውሰጃ (TP) ን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ የገበያ መዋዠቅን እና አደጋን የመቋቋም አቅምን መረዳትን ይጠይቃል።
